የወል ትርክትን በማጽናት አገር የያዘችው የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 13/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወል ትርክትን በማጽናት አገር የያዘችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሚና የላቀ መሆኑን የቀቤና ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ገለጸ፡፡
በቀቤና ልዩ ወረዳ “በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሚና እና የቀጣይ አቅጣጫዎች” በሚል መሪ ቃል ከሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
በቀቤና ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ የህያ ሀምዛ ብልጽግና ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ፓለቲካዊና ማህበራዊ የለውጥ ስራዎች በመስራት የዜጎች ህይወት እንዲሻሻል እና የአገሪቱ ገጽታ በአዎንታዊ መልኩ ተገንብቷል ብለዋል።
ብልጽግና በውስን ኃይልና በየግል ትጋት ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ኃላፊው የተሰሩ አጓጊ የለውጥ ስራዎች ሁሉም በየዘርፉ በተቀናጀ መንገድ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ቀጣይ በሚከናወኑ የለውጥ ስራዎች የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፉ ትኩረት በአዎንታዊ መንገድ በማህበረሰብ አብሮነት ላይ እና የተሰሩ የልማት ስራዎች ማጉላት ላይ መሆን አለበት ያሉት ኃላፊው እንደ ልዩ ወረዳ ከማህበረሰቡ በመቀናጀት በርካታ የልማት ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀቤና ልዩ ወረዳ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልናስር ሚፍታ በአገሪቱ እየተሰሩ ያሉ በርካታ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠንካራ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽ ስራ መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል።
በልዩ ወረዳው በተቀናጀ መንገድ በአዎንታዊ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራ ፈተናዎችን በድል በመቀየርና አፍራሽ አጀንዳዎችን በወል ትራክቶች በመመከት ረገድ ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተዋል።
በለውጡ መንግስት በርካታ ህዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የዜጎች ህይወት እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል።
የሀገር ግንባታን ለማፅናትና ሁለንተናዊ ስነ ተግባቦት ለመፍጠር የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሚና የላቀ ነው ያሉት ኃላፊው ሀሰተኛና ከፋፋይ ትርክቶችን በወል ትርክት በመመከት የማህበረሰቡን አንድነት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል።
በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የሚቃጡ የተዛቡ መረጃዎችን በመከላከል ኢትዮጵያ የያዘችው የብልጽግና ጉዞ መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊና ማህበራዊ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ውጤታማ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎች መጠናከር አለባቸው ብለዋል።
የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ልማትን ከማገዝ ባሻገር ለሰላም ግንባታ እየሰጠ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ በመሆኑ ዘርፉን በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ከፋፋይና ነጠላ ትርክቶች የሚያሰራጩ አካላት በመኖራቸው ሁሉም የሚመለከተው ባለድርሻ አካል በተረጋገጡ አቀራራቢ ሃሳቦች መመከት እንዳለበትም አሳስበዋል።
በውይይት መድረኩ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች እንዲሁም በማህበረሰቡ ዘንድ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ የማህበራዊ ማዲያ አንቂዎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ: አዱኛ ትዛዙ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

                
                                        
                                        
                                        
                                        
More Stories
ከ2 ሺህ በላይ አዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን መታቀዱን የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቃ
በኮሪደር ልማት፣ የመንገድ ግንባታ እና ተያያዥ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የጠቅላላ ተቋራጮች እና የአገልግሎት ተቋማት ትጋትና ቁርጠኝነት የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማህበራዊ ጫናዎችን ለመከላከል የኢኮኖሚ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላላት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለፀ