በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ የተመራ የክልሉ የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች ልዑክ የካራት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅንና የካራት ማረሚያ ቤት ግንባታን ጎበኙ
የሀገሪቱን የኮሪደር ልማት ውጤታማ ለማድረግ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የፈጠራ ስራቸውን ሊያጎለብቱ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ጠይቀዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ የተመራ የክልሉ የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች ልዑክ የካራት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅንና የካራት ማረሚያ ቤት ግንባታ ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝቱ ወቅት በዞኑ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ የቴክኒክና ሙያ ተቋሙ የድርሻውን እንዲወጣ የጠየቁት ዋና አፈ ጉባኤው፤ የካራት ከተማ የኮሪደር ልማትን የሚያግዘው የቴራዞን ማምረት ስራው አበረታች ስለመሆኑም አመላክተዋል።
በካራት ከተማ ማረሚያ ተቋም ባለመኖሩ ምክንያት ህብረተሰቡ ታራሚን ለመጎብኘት አርባምንጭና ዝዋይ በሚያደርገው ጉዞ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ሲዳረግ መቆየቱም ተነግሯል።
ይህ አዲሱ የካራት ማረሚያ ተቋም ግንባታ በህብረተሰቡና በመንግስት የጋራ ትብብር እየተገነባ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ በኃይሉ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ባለፉት አመታት የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርአትን በማዘመን የተሰሩ ስራዎች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ አስታወቀ
የጤናው ዘርፍ ተግባራት በኃላፊነት እና በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
በኮንታ ዞን የሽግግር ም/ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 26ኛው መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ