ሀዋሳ፡ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ በማዋልና ገዢ ትርክትን በማስረጽ በክልሉ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን ማስተዋወቅ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት አስታወቀ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማህበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ወጣቶች በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ የጠናቃ ድብር ጀፎረ ጎብኝተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት አብዱ ድንቁ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፥ ከክልሉ ባህል ቱሪዝም በጋራ በመሆን በማህበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ወጣቶችን የቱሪስት መስህቦች ለማስተዋወቅና ገዢ ትርክትን ለማስረጽ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለ6 ቀናት የቱሪስት መስህቦች ጉብኝት እየተካሄደ ይገኛል።
ገዢ ትርክትን በማስረጽና ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ በማዋልና በክልሉ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ክልሉን ለአለም ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ወጣቶቹ በክልሉ ካሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ መሆናቸውንና ጉብኝቱ የእርስ በእርስ ትስስራቸውን በማጠናከር የማህበረሰቡን ባህል ለማስተዋወቅ እነደሚረዳቸው አስታውቀዋል።
ጀፎረ የጉራጌ አባቶች ዘመናዊ ምህንድስና ባልነበረበት ዘመን በጥበብ ያቆዩት በመሆኑ ወጣቱም የአባቶቹን ፈለግ በመከተል ማስቀጠል እንደሚኖርበትና የገጠር ኮሪደር በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ሊተገበር ይገባል ነው ያሉት።
የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው በዞኑ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች መኖራቸውን ገልጸው ከእነዚህም ውስጥ ጀፎረ አንዱ መሆኑና የጉራጌ አባቶች የራሳቸውን ፍልስፍና ተከትለው ጠብቀው ያቆዩት ነው።
ጀፎረ ላይ የብሄር፣ የሐይማኖትና የጾታ እንዲሁም የኢኮኖሚ ደረጃ ልዩነት ሳይኖር ሁሉም የቀዬው ሰው እኩል የሚጠቀምበት እንዲሁም እድሜ ጠገብ የሆኑ ዛፎች መገኛም ጭምር መሆኑን አብራርተዋል።
ጀፎረ የመደመር፣ የአብሮነትና ህብረ ብሄራዊነትን በውስጡ ያቀፈ በመሆኑ የገጠር ኮሪደር ስራን በማጠናከር የተሻለ ጀፎረ እንዲኖር እንደሚሰራ አብራርተዋል።
የቸሀ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አንዳምላክ ይብጌታ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንዳሉት በወረዳው እጅግ ጥንት ከሚባሉና ማህበረሰቡ ጠብቆ ካቆያቸው መስህቦች መካከል ጀፎረ ሲሆን የሚዳኝበት ህግና መተዳደሪያ ደንብ አለው።
ወጣቶቹ በሰጡት አስተያየትም በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የቱሪስት መስህቦችን በመጎብኘት ላይ መሆናቸውና በክልሉ ያሉ የቱሪዝም ሀብቶችን ከመጎብኘት ባለፈ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
የጉራጌ አባቶች የምህንድስና ጥበብ የሆነው ጀፎረን በመጎብኘታቸው መደሰታቸዎን ገልጸው ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ በማዋል በክልሉ ያሉ የመስህብ ስፍራዎችና ሀብቶችን ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ መላኩ ንማኒ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የምክር ቤቶችን አቅም በማጎልበት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማጎልበት ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ ተናገሩ
በምግብ ሰብል ራስን የመቻል አቅም ማሳደግ ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
የበልግ አዝመራ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የእንሰት ችግኝ መተከሉ ተገለጸ