በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን በሚዛን ዲስትሪክት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የመብራት አገልግሎት አሰጣጥ ከተማው ከሚፈልገው የተገልጋይ ፋላጎት አንፃር ሊስተካከል እንደሚገባ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
ዲስትሪክቱ አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ በሚዛን አማን ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል።
በመድረኩም በኢትዮጰያ ከሚገኙ 32 ሪጅን ውስጥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።
በክልሉ ሪጅኑ የኘሮፎርማንስ ሞኒተሪንግ ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ አባይ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ጽሁፍ ሪጅኑ ከመስከረም 01/2017 ጀምሮ በአዲስ አሰራር ነድፎ በ18 የደንበኞች የአገልግሎት ማዕከላት በመጠቀም 185 ሳታላይት ጣቢያ አየተሠጠ ያለውን አገልግሎት አንስተዋል።
ከመብራት አገልግሎት አንፃር በርካታ የማስፋፊያ ስራ ተሰርቷል፡፡ መሻሻሎች ቢኖሩም ቀሪ የመብራት አገልግሎት አሰጣጥ ከተማው ከሚፈልገው የተገልጋይ ፋላጎት አንፃር ሊስተካከል እንደሚገባ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
በተለይ የመብራት መቆራረጥ፣ ያለአግባብ የቆጣሪ ንባብ፣ በኢንዱስትሪ መንደሮች የሀይል መቆራረጥ ላይ ትኩረት ማነስና ትራንስፎርመር በህብረተሰብ ተሳትፎ ጠይቆ ለማግኘት አለመቻል በቅሬታ ተነስተዋል።
የሪጅኑ መሠረተ ልማት ሀላፊ አቶ እስማኤል ሀብታሙ፤ በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሠጥተዋል።
የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ሰለሞን ለዊ፤ ከከተማዋ እድገትና የህዝብ ፍላጎት አንፃር እንደ መንግስት በመብራት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ስራዎች ውሰንነት ያላቸው ቢሆኑም በተለይ የኢንዱሰትሪ ማዕከላትና የህበረተሰቡን ጥያቄ መሰረት በማደረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ አሰረድተዋል፡፡
በመብራት የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በተዘጋጀው መድረክ ከሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የተደራጁ የወጣት ማህበራት አባላት፣ የየቀበሌ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ ሠለሞን አበበ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የተካሄደው 9ኛው የምስለ ችሎት ውድድር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
በማዕድን ሀብቶች ላይ ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ሥራ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ዉይይት እየተካሄደ ነዉ