የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ህዝብ የሚያነሳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ አመት 28ኛ መደበኛ ጉባኤው በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ነው።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ ኸይሩ መሀመድ መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት፥ በየደረጃው ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በዘላቂነት ለመፍታት አጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
በተለይም እንደ ሃገር ያጋጠሙ ፈተናዎችን በፅናት በመሻገር በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ተመላክቷል።
ከዚህም ባሻገር እንደ ሃገር የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፍ እየመጣ ያለው ውጤት ተስፋ ሰጪ በመሆኑ እነዚህ ተግባራት የሃገሪቱ የብልፅግና ጉዞ ማሳያዎች መሆናቸውን አቶ ኸይሩ ተናግረዋል።
በዞኑ በአንዳንድ አካባቢዎች የነበሩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት የተጀመሩ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አመራሩ በትኩረት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በበጀት አመቱ በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ የተያዙት ፕሮጀክቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ በትምህርት፣ በመንገድ፣ በውኃ፣ በመብራት መሰረተ ልማቶችና በግብርናው ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ እርካብነሽ ወ/ማርቆስ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን በሚዛን ዲስትሪክት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የተካሄደው 9ኛው የምስለ ችሎት ውድድር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
በማዕድን ሀብቶች ላይ ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ሥራ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ዉይይት እየተካሄደ ነዉ