በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የተካሄደው 9ኛው የምስለ ችሎት ውድድር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
በአስራ ሁለት ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል ለሶስት ቀን በተካሄደው የምስለ ችሎት ውድድር ባህር ዳርና ሰላሌ ዩኒቨርሲቲዎች ለፍጻሜ ቀርበው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያሸነፈ ሲሆን አዘጋጁ ሚዛን ቴፒ የኒቨርስቲ በ3ተኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡
ውድድሩ የሀገሪቱን የፍትህ ስርአትን ለማዘመን ሚናው የጎላ ከመሆኑ ባላይ ተሳታፊዎች ዕውቀትና ልምድ የሚለዋወጡበት እንደሆነም የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዋቆ ገዳ ተናግሯል ።
በእለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የፌደራል ህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ ውድድሩ በሀገሪቱ የፍትህ ችግርን ከመቅረፍ አንጻር የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በኩነቱ አንዱ ከሌላው ጋር እንዲተዋወቅ እና ራሱን ከሌላው ጋር እንዲያነጻጽር ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡
የውድድሩ አሸናፊ የሆነው የባህር ዳር የኒቨርስቲ የህግ ተማሪ ዮናስ ሙጨና የሰላሌ ዩኒቨርስቲ የህግ ተማሪ ሃዲስ አሜሪካው ውድድሩ አስደሳችና በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር ያሳዩበት እንዲሁም ትክክለኛ ችሎትን የሚመስል ገፅታ እንደነበረው ገልጸዋል፡፡
ለ9ኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች ምስለ ችሎት ውድድር አሸናፊዎችና ውድድሩ የተሳካ እንዲሆን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የሰርተፍኬትና ሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ዘጋቢ፦ በየነ ወርቁ ከሚዛን ጣቢያችን።
More Stories
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን በሚዛን ዲስትሪክት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በማዕድን ሀብቶች ላይ ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ሥራ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ዉይይት እየተካሄደ ነዉ