የጎፋ ዞን ዕድገትና ልማት ማህበር 5ኛ ቅ/ፍ ጽህፈት ቤቱን በይፋ ከፈተ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጎፋ ዞን ዕድገትና ልማት ማህበር በኣሪ ዞን ጅንካ ከተማ 5ኛ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን በይፋ ከፍቷል፡፡
የልማት ማህበሩ መመሥረት የህዝብን የእርስ በዕርስ ትስስር ይበልጥ በማጠናከር ዘላቂ ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ የማይተካ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል።
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም ኣታ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት የልማት ማህበራት የመንግስትን የልማት ክፍተቶች ከመሙላት አኳያ ሰፊ ድርሻ ያላቸው መሆኑን ጠቁመው፥ በጂንካ ከተማ የሚኖሩ የጎፋ ዞን ተወላጆች በከተማው ልማት ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
የጎፋ ዞን ልማት ማህበር በጂንካ ከተማ የከፈተውን ቅርንጫፍ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ አካባቢውን በልማት በማስተሳሰር የህዝቡን አንድነትና የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ መሥራት ይገባል ብለዋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መመሥረት የጋራ እሴቶቻችን በማቀናጀት በአብሮነት የምንቆምበት ዘመን መሆኑን የሚረዳ ትውልድ የመፈጠሩ ውጤት ነው ብለዋል።
በጂንካ ከተማ የሚኖሩ የጎፋ ዞን ተወላጆች ለቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ መመሥረት ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸውን አድንቀዋል።
የማህበሩ አባላት በልማት ማህበሩ የሚከናወኑ ልማቶችን ለይቶ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የጎፋ ዞን ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃ/ማሪያም ማህበሩ በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጪ በሚኖሩ የዞኑ ተወላጆች ድጋፍ በትምህርትና ጤናው ዘርፍ ሰፋፊ ሥራዎችን መሥራቱን አስታውሰዋል።
ተሳታፊ መሥራች አባላትም በሠጡት አስተያየት የልማት ማህበሩ በይፋ መመሥረት የረዥም ግዜ ህልማቸው እንደሆነ ተናግረው በቀጣይም የሚጠበቅባቸውን እንደሚያደርጉ ያላቸውን ተነሳሽነት ገልጸዋል።
የጎፋ ዞን ልማት ማህበር 5ኛ ቅርንጫፍ ሆኖ በይፋ የተመሠረተው ጽህፈት ቤት ስራ አስፈጻሚዎች ትውውቅ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን በሚዛን ዲስትሪክት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የተካሄደው 9ኛው የምስለ ችሎት ውድድር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ