በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ግንቦት 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ”የብልጽግና ጉዞዋችንና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና” በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር፤ ባለፉት አመታት የንግዱ ማህበረሰብ ሀገራችን ተጋርጦባት የነበረውን የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን በመጋፈጥ በድል ለመሻገር እያሳይ የነበረው ሚና ከፍተኛ እንደነበር ገልጸዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ የሚያደርገውን ተሳትፎ ይበልጥ በማጠናከር የልማት ጉዞዋችንን ማፋጠን ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል።
በንግድ ስርዓቱ ፍትሐዊ የግብይት ስርዓትን ለመፍጠር መንግስት ችግሮችን ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር በጋራ እየፈታ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የከተማው ማህበረሰብ ስራ ወዳድ፣ ሰላም ፈላጊ እና ከመንግስት ጎን በመሆን ልማትና ብልጽግና እንዲረጋገጥ አበክሮ የሚሰራ በመሆኑ ይህንን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።
በመድረኩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ታደሰ ዋጄቦ፣ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል፣ የዞኑ የሚመለከታቸው የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የከተማው አመራሮች እና የንግዱ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ደጋጋ ኂሳቦ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን በሚዛን ዲስትሪክት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የተካሄደው 9ኛው የምስለ ችሎት ውድድር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ