የወራቤ ዩንቨርሲቲ 3ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ግንቦት 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወራቤ ዩንቨረሲቲ ሶስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ተመራማሪ ምሁራን እንዲሁም የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት እያካሔደ ነው፡፡
የጥናትና ምርምሩ ኮንፈረንስ “ጥናታዊ ምርምር ለዘላቂ እድገትና ማህበራዊ ለውጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወራቤ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ኢንጂነር ቶፊክ ጀማል ባስተላለፉት መልዕክት የወራቤ ዩንቨረስቲ ከመማር ማስተማር ስራው በተጨማሪ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በምርምር ኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በትምህርት ስርዓቱ ውጤትን ለማሻሻል እና የትምህርት ስብራትን ለመጠገን መሥራት እንደሚጠበቅ ጠቁመው ማህረሰቡን ለመለወጥ የምርምር ስራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ: ሳጂዳ ሙዳስር – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
በክልሉ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራ አሳረፉ
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው
በክልሉ በተያዘው የበልግ ወቅት በኩታገጠም ሩዝና በቆሎ እያለሙ ያሉ አርሶአደሮች ተስፋ ሰጪ የሆነ የምርት ውጤት እንድናይ አስችሎናል አሉ።