በጋብቻ፣ ፍቺና ንብረት ክፍፍል የህግ ማዕቀፎች እና አተገባበር ዙሪያ ከክልሉ ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ዳኞች ስልጠና በአርባምንጭ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
የክልሉን ህዝብ የፍትህ ጥማት ለማርካትና ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት በተለይም በፍትህ ተቋማት የሚታዩ የክህሎት፣ የስነ-ምግባርና የአሰራር ክፍተቶችን ለማረም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 13/2016 ተቋቁሞ ወደስራ ገብቷል።
በዚህም የፍትህ ስርዓቱን ዘመናዊ፣ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚረዱ የህግ ጥናትና ምርምሮችን እያካሄደ እንደሚገኝ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ፍልፍሉ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ገልፀዋል።
አክለውም “ፍትህ በገንዘብ ይሸጣል” የሚለው ወቀሳና ትችት የፍትህ ባለሙያዎች ሁሉም የክህሎት፣ የአመለካከት እና የስነ-ምግባር ችግር ስላለበት ሳይሆን እንደባለሙያዎቹ ባህሪ እና አቅም ሁኔታ የሚንፀባረቁ ችግሮች መሆናቸውን ገልፀው የሚታዩ ችግሮችን ታግለን በማረም የተቋማችንን ክብር መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና የፍትህ እና ህግ ኢንስቲትዩት ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቦጋለ ፈይሳ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት፤ በጋብቻ፣ ፍቺና የንብረት ክፍፍል ዙሪያ ዳኞች በትኩረት መስራት አለባቸው።
ቤተሰብ የህብረተሰብ መሰረት፣ ህብረተሰብ ደግሞ የሀገር መሰረት መሆኑን ያወሱት አቶ ቦጋለ፤ ሀገርን ለመጠበቅ ሲባል ለቤተሰብ ህጉ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ከዳኝነት አካሉ እንደሚጠበቅ ገልጸው ስልጠናውን ወደ ተግባር መቀየር ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።
በጋብቻ፣ ፍቺና ንብረት ክፍፍል የህግ ማዕቀፎች እና አተገባበር ዙሪያ ከክልሉ ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ዳኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በክልሉ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራ አሳረፉ
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው
በክልሉ በተያዘው የበልግ ወቅት በኩታገጠም ሩዝና በቆሎ እያለሙ ያሉ አርሶአደሮች ተስፋ ሰጪ የሆነ የምርት ውጤት እንድናይ አስችሎናል አሉ።