የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 08/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) እንደሃገር እያጋጠመ ያለውን የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድርሻውን ሊወጡ እንደሚገባ የወልቂጤ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል ገለጹ።
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የስትራቴጂክ ጉዳይ ስራ አስፈጻሚዎች የምክክር መድረክ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
የምክክር መድረኩ የተሻለ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በዩንቨርስቲዎች መረጋገጥን አላማ ያደረገ ስለመሆኑም ተገልጿል።
ዩንቨርስቲዎች የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የሚያሻግር ትውልድ ማፍራት ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ከመድረኩ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የምክክር መድረክ 47 አባል ዩንቨርስቲዎች ያሉት ሲሆን በዋናነት በትምህርት ጥራት ላይ በአመቱ የተከናወኑ ስራዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው።
የዩንቨርስቲዎች የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈፃፃም ሪፖርት የተዘጋጀ ግብረ መልስ እየቀረበ ይገኛል።
በመድረኩም የወልቂጤ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል፣ ከትምህርት ሚኒስቴር የተወከሉ እንግዶች እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ አስቻለው አማረ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በክልሉ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራ አሳረፉ
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት 5ኛ አመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው
በክልሉ በተያዘው የበልግ ወቅት በኩታገጠም ሩዝና በቆሎ እያለሙ ያሉ አርሶአደሮች ተስፋ ሰጪ የሆነ የምርት ውጤት እንድናይ አስችሎናል አሉ።