በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በወላይታ ሶዶ ከተማ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው ከሃዋሳ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ የሚጠራ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡
በተከሰተው አደጋም የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ አስተዳደር ዋና ሳጅን ዝናቡ ገዛኸኝ ተናግረዋል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አቅራቢያቸው በሚገኙ ጤና ተቋማት ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑን ዋና ሳጅን ዝናቡ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ቅርንጫፍ
More Stories
ሀገራችንን ወደ ብልፅግና ለማድረስ የጽናት መንፈሳችንን ማደስ እንደሚገባ ተገለጸ
“ትንንሽ የሚመስሉ ስራዎች ለትልልቅ ዕድሎች በር ይከፍታሉ” – ወይዘሮ ህልውና ጌታቸው
የህግ ታራሚዎችን በስነ ምግባር ለማነፅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ገለፀ