የክልሉ መንግስት ከምን ጊዜም በላይ ህዝቡን ለማገልገል ዝግጁ ነው -ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የኢመዣር-ዱና -ሌራ የጠጠር መንገድ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ከምን ጊዜም በላይ ህዝቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት እና ፓርቲ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲጎለብት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዞኑ የጎሞሮ -ሙጎ -አይሳኮ መንገድ በዚህ አመት በቂ ዝግጅት በማድረግ በሚቀጥለው አመት ግንባታው እንደሚጀመር ርዕሰ መስተዳድሩ ቃል ገብተዋል።
ሌሎች የልማት ጥያቄዎችን አቅም በፈቀደ መጠን ምላሽ ለመስጠት የክልሉ መንግስት ዝግጁ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ በበኩላቸው የዞኑ ህዝብ ለመንገድ ልማት ካለው የላቀ ተነሳሽነት አንጻር የግንባታ ማሽነሪዎችን በመግዛት እንዲሁም ለተቋማት በኪራይ በማቅረብ ተሳትፎ ሲያደርግ እንደነበር ተናግረዋል።
በዞኑ መንገዶችን ከዋና መንገድ ጋር በማገናኘት የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ትኩረት ስለመሰራቱ ዋና አስተዳዳሪው አብራርተዋል።
ከመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች በተጨማሪ በጤና፣በትምህርት እና ሌሎች የኢኮኖሚ ተቋማት እውን እንዲሆኑ የዞኑ ህዝብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል
ምንጭ፡ የክልሉ መንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
More Stories
ገቢን በተገቢው በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በተገቢው መመለስ እንደሚገባ ተገለጸ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 የግብር ወቅት ከደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገለጸ
የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት የዘርፉን ተግባራት በተገቢው ለማሳካት ከምንጊዜውም በተሻለ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ