የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ክልላዊ መድረክ እየተካሄደ ነዉ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ክልላዊ መድረክ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በወላይታ ሶዶ እየተካሄደ ይገኛል።
”የመሃሉ ዘመንን መረዳት” በሚል ሃሳብ እየተካሄደ ባለው በዚሁ መድረክ፤ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ የተዘጋጀው ባለፉት ሰባት የለውጡ አመታት በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በቀጣይም በዘላቂነት ለማስቀጠል ነው።
መድረኩ በተለይ የህዝብን አንድነት በማጠናከርና ያሉትን ፈተናዎች ወደ ድል በመቀየር የሚፈለገውን ብልጽግና ለማረጋገጥ እንደሆነም ነዉ ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት።
የተመዘገቡት ስኬቶችን የበለጠ ዉጤታማ ለማድረግ አመራሩ ይበልጥ እንዲዘጋጁ የሚያስችል መድረክ መሆኑን አቶ ጥላሁን ጥላሁን ከበደ አስረድተዋል።
በመድረኩ “የመሐሉ ዘመን” በሚል ሃሳብ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ