የዞኑ ሕዝብ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ሀብታምነሽ ግራዝማች ባደረጉት የመግቢያ ንግግር፤ ምክር ቤቶች በሕገ-መንግስት የተሰጣቸውን ሥልጣን ተግባር እየፈፀሙ የዞኑ ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዞ እንዲፈጥን እንዲሁም የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን አብራርተዋል።
የምክር ቤቱ አባላት ያለፈውን 6ኛ አስቸኳይ ረቂቅ ቃለ ጉባኤ መርምረው አጽድቀዋል።
የምክር ቤቱ የ9 ወራት የሥራ ሪፖርት በዝርዝር ለአባላቱ የቀረበ ሲሆን የዞን፣የወረዳ፣የከተማና የቀበሌያት ምክር ቤቶች የመደበኛ ጉባኤ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ በጠንካራ ጎን ተገምግሟል።
የቋሚ ኮሚቴዎች ድጋፍና ክትትል በተመሣሣይ በጠንካራ ጎን ቢገለፅም በዞኑ በተለያዩ ዘርፎች የሚገኘውን አጠቃላይ የጥሬ ገንዘብ ዕዳ ከማስመለስ ረገድ ሰፊ ስራ የሚጠበቅበት መሆኑ ተመላክቷል።
ከኦዲት ግኝት ከማስመለስ አንጻር የታየው ደካማ አፈጻጸም በአስቸካይ ሊታረም እንደሚገባው በምክር ቤቱ አባላት አስተያየት ተሰጥቶበታል።
የጎፋ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የ9 ወራት ሪፖርት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤት ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚኖረው ቆይታ ልዩ ልዩ ሹመቶችን ምርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት የዘርፉን ተግባራት በተገቢው ለማሳካት ከምንጊዜውም በተሻለ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ