የህብረተሰብ ጤና ቅኝት ሥርዓትና የመረጃ ልዉዉጥ ማጠናከር በማህበረሰብ ላይ ሊከሰት የሚችል ወረርሽኝ ትርጉም ባለዉ መልኩ ለመከላከል ያግዛል – አቶ አንተነህ ፈቃዱ
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የህብረተሰብ ጤና ቅኝት ሥርዓትና የመረጃ ልዉዉጥ ማጠናከር በማህበረሰብ ላይ ሊከሰት የሚችል ወረርሽኝ ትርጉም ባለዉ መልኩ ለመከላከል እንደሚያግዝ ገለጹ።
የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራር አካላትና የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ክልላዊ የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ይፋዊ ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ይፋዊ ሥራ ማስጀመሪያ ወቅት እንደተናገሩት፤ የህብረተሰብ ጤና ቅኝት ሥርዓትና የመረጃ ልዉዉጥ ማጠናከር በማህበረሰብ ላይ ሊከሰት የሚችል ወረርሽኝ ትርጉም ባለዉ መልኩ ለመከላከል ያግዛል።
አክለዉም ለተቋሙ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት ምስጋና አቅርበዉ በቀጣይ ተቋሙን በማጠናከር ረገድ ድጋፋቸውን እንዲያጠናከሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላ በበኩላቸው፤ ተቋሙ በአዲስ መልክ በጥራት በተባበረ ደጋፊ በህብረተሰቡ ተሳትፎ መገንባትና ስራ መጀመሩ እጅግ እንደሚያስደስትና በቀጣይ በበለጠ በማደራጀት ሂደት የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ ድጋፉ እንደማይለይ ገልፀዋል።
ክልላዊ የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ይፋዊ ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር መድረክ የተለያዩ የመንግስትና ጥሪ የተደረገላቸዉ የህብረተሰብ አካላት በተገኙበት ዉይይት ተካሄዶ ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ወልደማርያም

More Stories
በሀገር በቀል ዕውቀት የሚታወቀውን የአካባቢውን እምቅ አቅም አጉልቶ በማሳየት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕድገት ማፋጠን እንደሚገባ ተገለፀ
በሩብ ዓመቱ ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምሎች እያስመረቀ ነው