የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ለአራት ክልሎች ስልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ለአራት ክልሎች ስልጠና ሰጠ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ለአራት ክልሎች የተዘጋጀ ስልጠና በአርባ ምንጭ እየሰጠ ነው።

የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ የተዘጋጀ የስልጠና አውደ ጥናትእና የተሞክሮ ልምድ ልውውጥ ለአራት ክልሎች የከተማ አሰተዳደር ከንቲባዎች በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ ባደርጉት የመክፈቻ ንግግር የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ የተለያዩ ተሞክሮዎችንና ያሉንን ልምዶች የምናካፍልበት መሆኑን ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ የከተሞች የእርስ በእርስ ትብብር እንዲጠናከር እና የኢትዮጵያ ከተሞች ከዉጭ ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አላማ አንግቦ የራሱን አስተዋፅኦ እየተጫወተ እንደምገኝ ተገልጿል።

በአጠቃላይ የትብብር መድረኩ 108 አባል ከተሞችን አቅም የያዘ አገልግሎት ለማስፋት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል ተብሏል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ዋና ዳይሬክተር አቶ አንዱዓለም ጤናው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የከተማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ የምስራች ገመዴን ጨምሮ ከማእከላዊ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከሲዳማ ክልል እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከተሞች ከንቲባዎች እና ባለድርሻ አካላት እየተሣተፉ ይገኛሉ።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስልጠና ያልተማከለ የፋይናንስ አስተዳደር ጽንሰ ሐሳብ እና ያልተማከለ የፋይናንስ ስርዓት ዓለም አቀፋዊ ፤ አህጉራዊና አገራዊ ተሞክሮዎች ፤ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ አሰባሰብ ተሞክሮ ላይ ገለጻ አንደምደረግ ታውቋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች የአርባ ምንጭ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ: ተዋበች ዳዲ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን