የፍትህ ተቋማት ቀልጣፋና ተደራሽ ፍትህን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተገቢው ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ
የጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ የህዝብ ምክር ቤት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የወረዳው ፍርድ ቤት እና የፍትህ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን አተገባበርን ገምግሟል።
የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አበበ አባይነህ በህዝብ አመኔታ ያለው ተቋም መገንባት እና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በፍትህ ተቋማት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
ከ2016 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የፍርድ ቤቶች ፍኖተ ካርታ እና የፍትህ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገበበት በመሆኑ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ይህን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አንስተዋል።
የጎፋ ዞን ደምባ ጎፋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የንገረ የደና ባለፉት ዘጠኝ ወራት የፍትህ ዘርፉ ውጤታማ፣ ታማኝና ግልጸኝነት በተላበሰ መልኩ በተገልጋዮች ዘንድ ያለውን አመኔታ ማሳደግ እንዲሁም አዳዲስ አዋጆችን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡
የደምባ ጎፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ድልነሳ ድዶ በበኩላቸው፤ የፍርድ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥን ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
የፍርድ ቤቶች ስራን ውጤታማ ለማድረግ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ተዘዋዋሪ ችሎቶችን አዘጋጅቶ ወደ ህብረተሰቡ ወርዶ ለመስራት ከበጀት እጥረትና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች መኖሩን አንስተዋል፡፡
ዘርፉን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የሕግ ማሻሻያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት የማህበረሰቡን ፍትህ አገልግሎትን ማሳደግ ላይ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
ደምባ ጎፋ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ አድማሱ የፍትህ ዘርፉን በተፈለገው ደረጃ ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
በፍርድ ቤቶች የሚታዩ አንዳንድ ክፍተቶች መኖራቸውን ያነሱት የውይይቱ ተሳታፊዎች በፍትህ አሰጣጥ ህብረተሰቡን ለማርካት በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንሚገባ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ ድጋፌ ድክሬ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን በሚዛን ዲስትሪክት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የተካሄደው 9ኛው የምስለ ችሎት ውድድር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ