ከተሞችን ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ገለፀ
መምሪያው የዘጠኝ ወራት አፈፃፀምና በቀጣይ ወራት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻዎች ጋር ውይይት በይርጋጨፌ ከተማ አካሂዷል፡፡
የጌዴኦ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሬድኤት ክፍሌ በመድረኩ እንደገለፁት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማ የውስጥ ለውስጥ አዳዲስ መንገድ በመክፈትና ነባሩን ለማስፋት በተደረገው ርብርብ በነቃ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተሞችን ለኑሮና ኢንቨስትመንት ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ያሉት ኃላፊው፥ በዞኑ የሚገኙ ከተሞች በፕላን እንዲመሩ ግልፅ፣ ቀልጣፋና ፍትሐዊ የመሬት አቅርቦትና አስተዳደር በማረጋገጥ ከተሞች ከአቻዎቻቸው እኩል ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መታየቱን የገለፁት የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የመምሪያው ምክትል ኃላፊና የማስፈጸም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ታደሰ ናቸው፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት የከተሞችን መሰረተ ልማት ለማስፋፋት የሚከናወኑ ተግባራትን ለመደገፍ የባለሀብቱና የህብረተሰቡ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን አቶ ብዙአየሁ ተናግረዋል፡፡
በአፈፃፀሙ የታዩ ጉድለቶችን በማረም የተጀመሩትን የልማት ስራዎችን አጠናክረው በመቀጠል ለከተማ ዕድገት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልጸው፥ በከተማ ጽዳትና ውበት እና በሌሎች ዘርፎችም ላይ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሪጅን በሚዛን ዲስትሪክት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የተካሄደው 9ኛው የምስለ ችሎት ውድድር በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ