ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የይዘት ዘርፍ ኃላፊ የተመራ የማናጅመንት ቡድን በማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ ያለውን አደረጃጀት እና አፈጻጸም ምልከታ አድርጓል፡፡
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የድርጅቱ ተወካይ አቶ ዘላለም ገነሞ 12ኛ ቅርንጫፍ ሆኖ በአጭር ጊዜ የተቋቋመውን የማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ ያለበትን የይዘትና አጠቃላይ አሰራር ሂደትን የጎበኙ ሲሆን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለሸካ ዞንና ለአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ለአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጭምር የመረጃ ምንጭ በመሆኑ ይህም የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ተቋማዊ ግንኙነትን በማጠናከር ተከታታይነት ያለው ድጋፍ እንደሚቀጥልና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከዋናው መስሪያ ቤት፣ ከክልሉ መንግስት እና ከዞኑ አስተዳደር ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
በቴክኖሎጂ የታገዘ ግንኙነት በማድረግ የተጀመረውን ተቋማዊ አሰራር ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር መሆኑን በዋናው ጣቢያ የሚዲያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተወካይና የስቱዲዮ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ታምሩ አስረድተዋል፡፡
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ናማሮ በበኩላቸው፤ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች የተናበበ ስራ ለመጣው ለውጥ አቅም መሆኑን አመላክተው ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የሚዲያ ተደራሽነትና የዜጎች መረጃ የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት ምላሽ እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያ ቅርንጫፉን ማደራጀት መቻሉን የጠቆሙት የጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ጎዱ፥ የዞኑ አስተዳደር በራስ አቅምና ሌሎች አጋዥ አካላት ላደረጉት ቀና ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በተቋሙ የዋናው መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ድርሻ ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ታምሩ፥ ዋናው መስሪያ ቤት ለቅርንጫፍ ጣቢያው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አስማማው ሀይሉ – ከማሻ ጣቢያችን

More Stories
በ6 ወራት ውስጥ ሊመዘበር የነበረ ከ156 ሚሊየን 560ሺህ ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የጉራጌ ክትፎ ባህልና እውቀትን በዩኒስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ እንደሚገኝ የኢፌዲሪ ቅርስ ባለስልጣን ገለፀ
በክልሉ ያሉ ብሔረሰቦችን ባህል ወደፊት በማውጣት የአካባቢውን ሰላምና ልማት ለማስቀጠል በትኩረት መስራት እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ተናገሩ