የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን አኗኗር ዘዬ የሚቀየር ተግባር መሆኑን በዳውሮ ዞን የከጪ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጠቅላይ ሚኒስትር ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረውን የገጠር ኮሪዶር ልማት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል።

የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ላይ አግኝተን ካነጋገርናቸው አርሶ አደሮች መካከል አቶ አኮ አምባ፣ ገዘኸኝ ገብሬ እና ታደለ ሀደሮ የከጪ ቱታ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ በተጀመረው የገጠር ኮሪደር ስራ ደስተኞች መሆናቸዉን ተናግረዋል።

አክለውም በአከባቢያቸው የሚገኙ አንደንድ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሌላቸው ዛፎችና ሌሎች ነገሮችን በማንሳት ለኑሮ ምቹ የሆነ አከባቢ ከመፍጠሩም በላይ ልዩ ውበት እየሰጠ መሆኑን ተናግሯል።

የተጀመረው የገጠር ኮሪደር ስራ በተሻለ ጥራት እንዲሠራና በተያዘው ጊዜ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንሚወጡ ነዋሪዎቹ ገልጿል ።

በወረዳው የተጀመሩ የገጠር ኮሪደር ስራ ለአርሶ አደሮች ኑሮ ምቹ እንደሆነ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሠሩ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ውለታው ሁሴን ጠቁመው፥ ሌሎች አከባቢዎችን የሚያገናኝ 25 ኪ.ሜ የገጠር ኮሪደር ስራ ለመስራት ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን አስተዳዳሪው አክለው ገልጸዋል።

ዘገቢ፡ አፈወርቅ ኦሹ – ከዋካ ጣቢያችን