በትምህርት ጥራት መሻሻል ላይ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በመማር ማስተማርና ተግባቦት ያለው ድርሻ ጎላ በመሆኑ የመምህራንን አቅም በማሰደግ ዩኒቨርሲቲዎች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀምና ሌሎች የአከባቢ ቋንቋዎችን ለማሳደግ ያለመ ስልጠና ከኣሪና ከደቡብ ኦሞ ዞን ከተመረጡ ወረዳዎች ለተውጣጡ እንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን በደቡብ ኦሞ ዞን ቀይ አፈር ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።
መምህራን የእንግሊዝኛው ቋንቋን ጨምሮ በሌሎች መግባቢያ ቋንቋዎች ከተማሪዎች፣ ከትምህርት ተቋማትና ከሙያቸው ጋር ያለውን ግንኙነት በስነ ምግባር እንዲመሩ እንዲሁም ንቁና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተመልክቷል።
በዩኒቨርስቲውም ማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰው ኮሌጅ ዲን መምህር አብርሃም ዮሐንስ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የመምህራንን አቅም መጎልበት ሚና እንዳለው በማመን ዩኒቨርስቲው በኣሪ ዞንና በደቡብ ኦሞ ዞን በተመረጡ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ያሉ የእንግሊዝኛ መምህራን በትምህርት አሳጣጥና በተማሪዎች ትምህርት አቀባበል ሂደት መካከል ያለውን ጉድለት ለመሙላት የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
መምህር አብርሃም አክለው በሀገሪቱ የተጀመሩትን የትምህርት ጥራት ለመሻሻል የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢያዊ ቋንቋዎች ላይ የጥናትና ምርምር ተግባራትን በመከናወን የተሻለ ዕውቀትና የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ ዩኒቨርስቲው እየሰራ ነው ብለዋል ።
ስልጠናውን ከሰጡ መምህራን መካከል በዩኒቨርስቲው የስነ ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት መምህርና የትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር አንዱአለም ግርማ በተቋሙ ከሚከናወኑ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት አንዱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ መምህራን የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻልና በስነ-ምግባራቸው የተሻሉ እንዲሆኑና መምህራን ለተማሪዎች ሞዴል በመሆን ጥሩ ዜጋ ለማፍራት የሙያ ተግባራቸውን የሚያከናውኑበትን መንገድ የሚያሳይ ስልጠና ነው ብለዋል።
ስልጠናውን ያገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ ትምህርት መምህራን ዩኒቨርስቲው ለትምህርት ማሻሻል በመምህራን አቅም ግንባታ ላይ እያደረገ ያለውን ጥራት አድንቀው በቀጣይም ሰፋ ባለ መልኩ ለሌሎች ትምህርት ዘርፍ መምህራን ተከታታይ ስልጠና በመስጠት በተማሪዎች ውጤት ላይ የተሸለ ለውጥ ለማምጣት እንዲሰራ ጠይቀዋል ።
ዘጋቢ፡ ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ቀልጣፋ የመንገድና ትራንስፖርት አገልግሎት በለለበት ልማትን ማሳለጥ የሚቻል ባለመሆኑ፣ የገጠር መንገድ
የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በሸማቾች ማህበር የሚቀርቡ ምርቶች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ሸማቾች ተናገሩ
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 ዓ.ም የተገልጋይ ውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው