ድልና ውጤት የሚመጣው በምኞት ሳይሆን ጠንክሮ በጋራ መሥራት ሲቻል ነው ሲሉ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ ተናገሩ

ድልና ውጤት የሚመጣው በምኞት ሳይሆን ጠንክሮ በጋራ መሥራት ሲቻል ነው ሲሉ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ ተናገሩ

“ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ቃል የለውጡ መንግስት የተመሰረተበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ክላስተር ማዕከል የመጋቢታዊያን የብልጽግና ፍሬዎች መድረክ  እየተካሄደ ይገኛል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ህዝብን የሚያደምጥ ፖለቲካ በሀገራችን ውስጥ ማቆጥቆጥ በመጀመሩ ለውጥ ማየት ችለናል ያሉት  የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ባለፉት ሰባት ዓመታት ሀገሪቱን ከመደናበር መንገድ አውጥተን ወደ ዕድገት ሀዲድ እንድትገባ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር ) መንግስት በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ  ባለፉት ሰባት ዓመታት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸው የተመዘገቡ ድሎች በላቀ ቁርጠኝነት ተባብረን ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል።

ባለፉት ሰባት ዓመታት በመንግስት የተጀመሩ ትላልቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን በመግለጽ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግራችን በማንበብና በማየት ብቻ የሚመለስ ባለመሆኑ ፖሊሲ ቀርጾ ትኩረት በመስጥት ተሠርቷል ያሉት ዶ/ር መሪሁን ድልና ውጤት በምኞት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ጠንክሮ በጋራ ርብርብ መሥራት ሲቻል መሆኑን አመላክተዋል።

ዘጋቢ ፡ ውብሸት ካሣሁን-ከይርጋጨፌ ጣቢያችን