በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ

በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ

በልዩ ወረዳዉ “የመጋቢታዊያን የለዉጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል ባለድርሻ አካላት በተኙበት የፓናል ዉይይት በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ እንደገለፁት የብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት ዉስብስብ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ፈተናዎችን በድል በመወጣት በአገር አቀፍ ደረጃ ተጨባጭ ለዉጦችን አምጥቷል።

የቀቤና ህዝብ ለበርካታ አመታት ሲጠይቅ የነበረዉ የመዋቅር ጥያቄ ምላሽ ያገኘዉ ባለፉት የለዉጥ አመታት መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪዉ የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በአጽንኦት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አቡበክር ዱላ በበኩላቸዉ በአገሪቱ ለዉጡን ተከትሎ የመጡ ችግሮች እንደነበሩ በማስታወስ ፓርቲዉ ችግሮቹን ወደ ድል በመቀየር በርካታ ለዉጦችን ማምጣቱን አስገንዝበዋል።

በአንዳንድ አከባቢዎች የሚታዩ የሰላምና የፀጥታ ችግሮችን በመፍታትና ጥራት ያለዉ የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የህብረተሰቡን ልማታዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ፓርቲዉ በዘላቂነት እንደሚሰራም ሀላፊዉ ገልፀዋል።

በፓናል ዉይይቱ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የልዩ ወረዳዉ ምክትል አስተዳዳሪና የፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብድልማሊክ አብደላ ፓርቲዉ ከተመሰረተ 2010 ዓ.ም ጀምሮ በአገሪቷ ሁሉም አከባቢዎች ያስገኛቸዉ ለዉጦች ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል።

በግብርናዉ፣ በማኒፋክቸሪንግ፣ በእንዱስቱሪዉ፣ በቱሪዝምና በሌሎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ለዉጦች ተጠቃሽ መሆናቸውን አብራርተዋል።

አስተያየታቸዉን የሰጡት የፓናል ዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ እለቱ ለኢትዮጵያዊያን ታሪካዊ ቀን መሆኑን በማንሳት የለዉጡ አመታት ሊታዩ የሚችሉ ለዉጦች የመጡበት በተለይ የወጣቶች እና የሴቶች ተጠቃሚነት ይበልጥ ፍሬ ያፈራበት መሆኑን አንስተዋል።

ለዉጡን ለማስቀጠል የበኩላቸዉን ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸዉንም ተናግረዋል።

በመድረኩ የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አፈጉባኤ አቶ ፈቱዲን ሙዘሚል፣ የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ፣ የልዩ ወረዳዉ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አቡበክር ዱላ፣ የልዩ ወረዳዉ የስራ አስፈፃሚ አካላት፣ የስራ አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ተከናዉኗል።

ዘጋቢ ፡ ሪያድ ሙህዲ- ከወልቂጤ ቅርንጫፍ