የመጋቢት ፍሬዎች ትናንት፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና በሚል መሪ ቃል በማረቆ ልዩ ወረዳ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

የመጋቢት ፍሬዎች ትናንት፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና በሚል መሪ ቃል በማረቆ ልዩ ወረዳ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ: መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማረቆ ልዩ ወረዳ የመጋቢት ፍሬዎች ትናንት፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና በሚል መሪ ቃል ባለፉት ሰባት አመታት የተመዘቡ የለውጥ ፍሬዎችን የሚዘከር የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

የልዩ ወረዳው አስተዳዳሪ ጀማል አማሮ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት መጋቢት ወር ትልቅ ትርጉም ያለውና የማረቆ ህዝብ በተፈጠረው የልዩ ወረዳ አስተዳደር አማካይነት ህዝቡ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ችሏል ብለዋል።

በአከባቢው ሰላም ለማስፈን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ጠቁመው በዚህም ውጤት መጥቷል ብለዋል። ህዝቡም ከመንግስትና ገዢው ፓርቲ ጋር በጋራ ሰላምን የማፅናት ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

ሃገራዊ ፖለቲካዊ ለውጡ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፥ አጋር ፓርቲዎች በብልፅግና አማካይነት ወደእኩል ውሳኔ ሰጭነት መምጣት መቻላቸው የሚጠቀስ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህ መድረክ ባለፉት ሰባት አመታት በመንግስትና በፓርቲ የተከናወኑ ተግባራት ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ሲሆን፥ ከፓናል ውይይቱ ጎን ለጎን የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በመድረኩ የማረቆ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ባለሙያዎች ፣ የሐይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው፡፡

ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ