“ትላንት፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ቃል በቡታጅራ ከተማ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ: መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ “ትላንት፣ ዛሬና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ አመራር እና አባላት የማጠቃለያ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
ባለፉ ሰባት አመታት የተመዘቡ የለውጥ ፍሬዎችን የሚዘከር እና በሚያጋጥሙ አሁናዊ ፈተናዎች ዙሪያ የሚመክር የማጠቃለያ ፓናል ውይይት ‘ትላንት፣ ዛሬና ነገ’ በሚል ርዕስ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊና የቡታጅራ ክላስተር የብልጽግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ዳምጠው የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም እውን የሆነውን ሀገራዊ ለውጥ 7ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ አመራር እና አባላት የማጠቃለያ የፓናል ውይይት መካሄድ ጀምሯል ።
በመድረኩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የቡታጅራ ከተማ ክላስተር ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሙያዎች ፣ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው፡፡
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ
ድልና ውጤት የሚመጣው በምኞት ሳይሆን ጠንክሮ በጋራ መሥራት ሲቻል ነው ሲሉ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ ተናገሩ
መጋቢት 24 በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ የፖለቲካ እጥፋት የተደረገበት ነው – ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ