የመጋቢት 24 በዓል በጂንካ ከተማ እየተከበረ ይገኛል

የመጋቢት 24 በዓል በጂንካ ከተማ እየተከበረ ይገኛል

ሀዋሳ፡ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማህበራዊ ክላስተር ጂንካ ማዕከል፣ ኣሪ ዞን እና ጂንካ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ህብረት አባላት የመጋቢት 24 በዓልን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ ይገኛል።

በአከባበሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍና የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ኢንጅነር ፍሬዘር ኮርባይዶ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የኣሪ ዞን እና የጂንካ ከተማ አመራርና ፓርቲ አባላት እየተሣተፉ ይገኛል።

አከባበሩ በፎቶ ኤግዝቢሽንና የጂንካ ከተማ ኮሪደር ልማት ጉብኝት እየተደረገ ይገኛል።

ዘጋቢ፡ መልካሙ ቡርዝዳቦ – ከጂንካ ጣቢያችን