“ብልፅግና እና ሰው ተኮር ስራዎች በሚል መሪ ቃል “በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃድያ ዞን በሆሳዕና ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ የመጋቢት ወር የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል
የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት ከከተማው መሰራተ ልማት ዕቅዶች መካከል የሰንበት ገበያን ማስፋፋት እና የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት አንዱ ሲሆን፣ በዛሬው እለትም አስራ ሶስተኛውን የሰንበት ገበያ በሊች አምባ ቀበሌ ማስጀመር ተችሏል ።
በከተማው ናራሞ ቀበሌ የ45 ቀን የጫጩት እንዲሁም የወተት ከብት እርባታ ስራዎች ምልከታ የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም ከስደት ተመላሽ ወጣቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በከተማው የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራ በሁለት ወር ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።
የሀድያ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ በበኩላቸው በጉብኝቱ ወቅት በተመለከቱት የልማት ስራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፣ የተጀመሩ ስራዎች በሀገር ዕድገት ላይ ያለው አስተዋፆ ጉሊህ መሆኑን በማንሳት፣ ሁሉም የልማት ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
በሊች አምባ ቀበሌ የምስራቅ በር አንደኛ ደረጀ ት/ቤት የተማሪዎች የምገባ ዝግጅት ምልከታ በማድረግ የት/ቤቱን የምገባ ፕሮግራሙን ከፍተኛ የስራ አመራሮቹ በተገኙበት አስጀምረዋል።
በጉብኝቱም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳድር አማካሪ አቶ ንጉሴ አስረስ፣ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽንጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን እሼቱ ፣የሀድያ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ፣ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደዊት ጡምደዶና ሌሎች የክልል፣ የዞንና የከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ ፡ ሳምራዊት ያዕቆብ -ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
በሀገሪቷ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ገለፁ
ድልና ውጤት የሚመጣው በምኞት ሳይሆን ጠንክሮ በጋራ መሥራት ሲቻል ነው ሲሉ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ ተናገሩ
መጋቢት 24 በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ የፖለቲካ እጥፋት የተደረገበት ነው – ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ