የለውጡ መንግስት ያስመዘገባቸውን ድሎችን በላቀ ሀላፊነትና ቁርጠኝነት ልናስቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ

የለውጡ መንግስት ያስመዘገባቸውን ድሎችን በላቀ ሀላፊነትና ቁርጠኝነት ልናስቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ

‎ይህ የተባለው “ትላንት፣ ዛሬንና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ቃል የአርባምንጭ ክልል ማዕከል ኢኮኖሚ ቁጥር 1 የብልጽግና ህብረት የመጋቢት 24 ቀን በዓል መድረክ ላይ ነው፡፡

‎በአርባምንጭ ማዕከል በተዘጋጀው መድረክ ተሳታፊ የሆኑ አካላት መንግስት በለውጡ ዓመታት በርካታ ፈተናዎችን ተጋፍጧል ብለዋል።

‎የኑሮ ውድነቱንና የነዳጅ አቅርቦትን ከማሻሻል አንፃርም በቀጣይ ቀሪ ተግባራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

‎በመጋቢት ወር የተበሰረው ብስራት ፓርቲው በሂደቱ ያደረጋቸው ተጋድሎዎች ውጤት ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ መመዝገቡም ተመላክቷል።

‎በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ ሀይል አቅርቦቱ ዘርፍ መሰረት የተጣለበት በመጋቢት 24 እንደሆነና በዚህም ሀገራችን ለውጥ ማስመዝገቧን አውስተዋል።

‎መንግስት በከተማ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተጨባጭ ተግባራትን ከማከናወኑም ባሻገር የዲጂታል ኢኮኖሚን ተግባራዊ ማድረግ መቻሉ የሚታዩና የሚጨበጡ ለውጦች አሉም ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

‎በሀገራችን ተግባራዊ የተደረገው ሪፖርትም ጥልቅ፣ ተጨባጭ እና አካታች እንደሆነ ያወሱት ተሳታፊዎቹ፤ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ ለውጥ እንዲመዘገብ ማድረጉን አብራርተዋል።

‎ውጤቶች እንዳሉ ሁሉ ድጋፍ የሚሹ ተግባራት እንደሚገኙ ያብራሩት ተሳታፊዎቹ ያሉንን ፀጋዎች ተጠቅመን የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመፍታት ሁሉም በባለቤትነት ሊንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

‎የለውጡ መንግስት እንዲወለድ ያደረገው ምክንያት የሰላም እጦት መሆኑን ጠቁመው ሰላሙን ለማስጠበቅ ብዙ መስዋዕትነት መከፈሉንና በቀጣይም ሰላምን ለማረጋገጥ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን፤ የለውጡ መንግስት ያስመዘገባቸውን ድሎች በላቀ ሀላፊነትና ቁርጠኝነት ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል።

‎ሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት የሚቃጣባትን ጫና ተቋቁማ ማለፍና መመከት መቻሏን የተናገሩት ወ/ሮ ሰናይት፤ በፀጥታ ተቋማት እያደገ የሚሔድ ሀይል መገንባቱንና ችግሮችን በተጨባጭ መፍታት መቻሉን ጠቁመዋል።

‎በሀገራችን ጉዳይ ላይ ሁላችንም እኩል ሀላፊነት ያለብንና በሀገረ መንግስት ግንባት ከማጠናክርና ተሳትፎነታችንን ማጠናከር ይጠበቅብናል ያሉት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ ናቸው።

‎የለውጡ ጅማሬ ከመበሰሩ በፊት የነበሩ ችግሮችን በጥበብ ያለፍንበትና እንደሀገር የቀጠልንበትን አኩሪ ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል ያሻል ብለዋል።

‎ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን