የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በነገው ዕለት መካሄድ ይጀምራል
20ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በነገው ዕለት በቻይና ናንጂንግ ከተማ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ሻምፒዮናው በ12 አትሌቶች ትወከላለች፡፡
በሻምፒዮናው የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ትናንት ከሰዓት በኋላ ወደ በስፍራው መድረሱ ይታወቃል።
በውድድሩ በ5 ርቀቶች ላይም ኢትዮጵያ የምትወከል ይሆናል።
በዚህም መሰረት በ800 ሜትር ሴቶች አትሌት ፅጌ ዱጉማ፣ ሀብታም ዓለሙ እና ንግስት ጌታቸው ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።
ጉዳፍ ፀጋይ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ወርቅነሽ መለሰ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የሚሳተፉ አትሌቶች ናቸው።
ፍሬወይኒ ኃይሉ እና ብርቄ ኃየሎም በሴቶች የ3000 ሜትር ውድድር ላይ ተሳታፊ ናቸው።
በወንዶች በሪሁ አረጋዊ፣ ቢኒያም መሐሪ እና ጌትነት ዋለ በ3000 ሜትር ወንዶች ውድድር ላይ ይወዳደራሉ።
አትሌት መለሰ ንብረት በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ላይ ይሳተፋል።
በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ላይ ስሙ ተካቶ የነበረው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በህመም ምክንያት ከቡድኑ መቀነሱም ተገልጿል።
ለ3 ቀናት በሚቆየው ተወዳጅ ውድድር ኢትዮጵያ በመክፈቻው ቀን በ800 ሜትር ሴቶች እና በ1500 በሁለቱም ፆታ የማጣሪያ ውድድሮች የምትካፈል ይሆናል።
በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ከ127 ሀገራት የተውጣጡ ከ570 በላይ አትሌቶች እንደሚሳተፉ የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያስረዳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው