ለአርሶና አርብቶ አደሮች ቴክኖሎጂን ተደራሽ በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 08/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለአርሶና አርብቶ አደሮች ቴክኖሎጂን ተደራሽ በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ገለፀ።
ኢንስቲትዩቱ ዓመታዊ የምርምር ሥራ ክንውን ግምገማ ከዩኒቨርስቲዎችና ከምርምር ተቋማት ከተወጣጡ ምሁራንና ባለድርሻ አካላት ጋር በዲላ ዩኒቨርሲቲ እያካሄደ ነው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ለአርሶ አርብቶ አደሮች ቴክኖሎጂን ተደራሽ ለማድረግ በክልሉ አርባምንጭ፣ አረካና ጂንካ ቀድሞ በነበሩት ምርምር ማዕከላት ይርጋጨፌና ሳውላ በመጨመር የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠሩ መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ያሲን ጎኣ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ከዩኒቨርስቲና ምርምር ተቋማት መሪ ተመራማሪዎች ጋር በመቀናጀት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም የተሻለ ውጤት ለማምጣት እየተጋ ነው ያሉት ኃላፊው፥ ከመጋቢት 8 እስከ 12/2017 ዓ/ም ዓመታዊ የምርምር ሥራ ክንውን ግምገማ ከዩኒቨርስቲዎችና ከምርምር ተቋማት ከተወጣጡ ምሁራንና ባለድርሻ አካላት እያካሄደ መሆኑን ምክትል አስታውቀዋል፡፡
ዘመናዊ ግብርናን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የግብርና ምርምር ማዕከላት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የገለፁት በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊና የዲላ ክላስተር አስተባባሪ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር)፥ የግብርና ምርምር ማዕከል እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር) የሚሠሩ ጥናቶችን ወደ ተግባር በመለወጥ የማህበረቡን ችግር በመቅረፍ የምርምር ተቋማት ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ከወትሮ ይበልጥ ተቀራርበው እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ሕብረተሰቡ ቀልጣፋና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን እንዲያገኝ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መሥራት እንደሚገባቸው ተገለፀ
አሰቃቂ የግዲያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት
ምክር ቤቶች በአገር ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ጉዞዎችን አጠናክርው ማስቀጠል እንደሚገባቸው ተገለጸ