ሕብረተሰቡ ቀልጣፋና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን እንዲያገኝ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መሥራት እንደሚገባቸው ተገለፀ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 08/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መሥራት እንደሚገባቸው ገለፀ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 ዓ.ም የግማሽ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በዲመካ ከተማ አካሂደዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተወካይና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መልካሙ ሺበሺ የአፈፃም መድረኩን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት፥ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን አፈፃፀም በዞኑ ዝቅተኛ በመሆኑ ለአፈፃፀሙ ተግዳሮቶችን በመለየት በአጭር ጊዜ ሥራውን ውጤታማና የተሳካ እንዲሆን የጋራ ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አሰፋ በአፈፃፀም በበኩላቸው፥ ለማህበረሰቡ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የተከናወኑ ተስፋ ሰጪ ተግባራትን ለማጠናከር ባለድርሻ አካላት ይበልጥ ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል።
የመድኃኒት አቅርቦትን ማሻሻል፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል እና የሕክምና መሣሪያዎችና ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር ያሉ ክፍተቶችን በማረም የሕብረተሰቡን ጤና የመጠበቅ ሥራዎችን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።
የእናቶችና ሕፃናት ሞት ለመቀነስ በሰለጠነ ባለሙያ የወሊድ አገልግሎት መስጠትና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ትኩረት በንቅናቄ ሊመራ እንደሚገባ አቶ ታምራት አሳስበዋል።
የዞኑን የግማሽ አመት የጤና ሥራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ለታዳሚው በዞኑ ጤና መምሪያ የጤና ልማት ዕቅድ ቡድን መሪ አቶ ታደለ ተገኝ ሰነድ ቀርቦ የጋራ ውይይትም ተደርጓል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ለአርሶና አርብቶ አደሮች ቴክኖሎጂን ተደራሽ በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አሰቃቂ የግዲያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት
ምክር ቤቶች በአገር ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ጉዞዎችን አጠናክርው ማስቀጠል እንደሚገባቸው ተገለጸ