ምክር ቤቶች በአገር ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ጉዞዎችን አጠናክርው ማስቀጠል እንደሚገባቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 08/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ምክር ቤቶች በአገር ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ጉዞዎችን አጠናክርው በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ የሸኮ ወረዳ ምክር ቤት አስታወቀ።
የወረዳው ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ በመሀል ሸኮ ከተማ እያካሄደ ነው።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አሰፋ ሸዋ እንደገለፁት ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ ከመሆናቸውም ባለፈ በአገር ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ጉዞዎችን አጠናክርው በማስቀጠል የህዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተናገረዋል።
የምክር ቤት አባላት ወረዳውን በማልማትና ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደረጉ አገለግሎቶችን በመስጠት ረገድ ኃላፊነታቸውን በታማኝነት እንዲወጡ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አቶ አሰፋ አስረድተዋል።
በህዝቡ ውስጥ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመፍታት የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማሻገር የምክር ቤት አባላት ኃላፊነታቸውን አጠናክረው ሊቀጠሉ እንደሚገባም አፈ ጉባኤው ገልፀዋል።
በወረዳው የተጀመረውን ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምና ብልፅግና በማረጋገጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ሁሉም በተሰማራበት መስክ መስራት እንደሚገባ አቶ አሰፋ አፅንኦት ሰጥቷል።
የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ጌታቸው ኮምቱ የ2017 የ2ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤት ጉባኤ አባላትና ተሳታፊዎች ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት፥ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ እንደመሆናቸው መጠን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በመንግስት አሰራር ላይ የህዝብ ተሳትፎን በማረጋገጥ ረገድ የድርሻውን ሲወጣ መቆየቱን ተናገረዋል።
በቀረበው ሰነድ ላይ በትምህርት ቤቶች አፈፃፀም፣ በሚዲያ አጠቃቀም፣ ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ በሚታዩ ችግሮችና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ የምክር ቤት አባላት አስተያየትና ጥያቄ በማንሳት ውይይት ተደረጎበታል።
በተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ የሚተገበሩ ጉዳዮችን በመውሰድ እንደሚሰሩም ገልፀዋል።
ጉባኤው በሚኖረው ቆይታ የምክር ቤትና የወረዳ አስተዳደር አስፈፃሚ ተቋማት እንዲሁም የፍርድ ቤት የ2017 በጀት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በመገመገም እና የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም ከወጣው መረሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
ለአርሶና አርብቶ አደሮች ቴክኖሎጂን ተደራሽ በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሕብረተሰቡ ቀልጣፋና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን እንዲያገኝ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መሥራት እንደሚገባቸው ተገለፀ
አሰቃቂ የግዲያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት