ሀዋሳ፡ መጋቢት 01/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የምክር ቤቱ አባላት የህዝብን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰሩ ያሉት ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ መምጣታቸውን የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት ገለፀ።
የዞኑ ምክር ቤት 4ኛ አመት 12ኛ ዙር 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጌዲዮን ኮስታብ፤ ምክር ቤቱ የዞኑ ህዝብ ሉአላዊነት መገለጫ በመሆኑ ፈጣን ልማት፣ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ለመልካም አስተዳደር መስፈን ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
ስለሆነም የምክር ቤቶችን የመወሰን አቅም በማሣደግ ለዞኑ ህዝብ ተጠቃሚነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳያና እያደገ መምጣቱንም አመልክተዋል።
ምክር ቤቱ አባላት በመንግስት አካላት የታቀዱ፣ ህግ የማውጣት፣ የማስፈፀምና የመተርጎም ስራዎች በታቀደው ልክ ተግባራዊ ተደርገው የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል የተሰጣቸውን የህዝብ ሀላፊነት እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ለህዝብ ኑሮ መሻሻል ያበረከቱት ድርሻ ለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የሚያግዙ ተግባራት መከናወናቸውን በመከታተልና በማረጋገጥ የበኩላቸውን ሚና በመጫወት ላይ ስለመሆናቸው ገልፀዋል።
በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶችን በመደገፍና በማብቃት ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ጥቆማዎችን በመቀበል፣ በማጣራት፣ ምላሽ በመስጠትና የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮችን በማዘጋጀት በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲሰጥባቸው በማድርግ የህዝቡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ እያደረገ መሆኑን አፈ ጉባኤው ጌዲዮን ኮስታብ ተናግረዋል።
ለሁለት ቀናት የሚቆየው የምክር ቤቱ ጉባኤ በዞኑ እየተከናወኑ የሚገኙ ልማቶችን ከመጎበኘት ባሻገር የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የግማሽ አመት የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ አሳሳኸኝ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የተከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር የልምድ ልውውጥ ተደረገ
ሳታ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ በአርባ ምንጭ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ
በዕቅድ የሚመራ የመፈፀም አቅሙ ያደገ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ገለፀ