የከተሞችን የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በማከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አስታወቀ

የከተሞችን የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በማከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አስታወቀ

የከተሞችን የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች በመሆናቸው በቀጣይ መሰል የልማት እንቅስቃሴዎችን በማገዝ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የከተሞችን የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተማም አወል ተናግረዋል፡፡

በመንግስት እና በሕብረተሰብ ትብብር ያለምንም ካሳ ክፍያ በበጀት ዓመቱ 3 ነጥብ አምስት ሚሊያን ብር የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መሠረተ ልማት ተደራሽነትን ለማስፋፋት በተሰራው ሥራ 10 ኪሎ ሜትር የመንገድ ከፈታ እና 12 ኪሎ ሜትር የመጠገንና ጠጠር የማልበስ ሥራ መሰራቱንም ገልፀዋል፡፡

ከኢንቨስትመንት መሬት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ መቻሉንም አመላክተዋል፡፡

በሚሰሩ የልማት ሥራዎች የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ነው ያሉት ኃላፊው፤ በቀጣይም በኮሪደር ልማት መነሻ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየተሰሩ ያሉ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መሠረተ ልማት ተደራሽነት ሥራን አጠናክሮ ለማስቀጠል እቅድ መያዙን ጠቁመዋል፡፡

የሌራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙባሪክ አክመል በበኩላቸው፤ እንደ ከተማው በሦስት ሚሊያን ብር የመንገድ ከፈታ እና ጠጠር የማልበስ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

መሠረተ ልማትን ተደራሽ ማድረግ በመንግስት ብቻ የማይቻል በመሆኑ ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የመንገድ መሠረተ ልማት ለማረጋገጥ እና መሰል የልማት ሥራዎች በጋራ እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

የከተሞች የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች በመሆናቸው በቀጣይ መሰል የልማት እንቅስቃሴዎችን በማገዝ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ያነጋገርናቸዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የመብራት እና የመንገድ መሠረተ ልማት ሥራዎች መሰራታቸው ምቹ የአኗኗር ሁኔታን ከመፍጠር በተጨማሪ ህብረተሰቡ ለሚያከናውናቸው የልማት እንቅስቃሴ ስኬት ወሳኝ ናቸው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ሳጅዳ ሙደስር – ከሆሳዕና ጣቢያችን