ኤር ማሮክ የተባለው የሞሮኮ አየር መንገድ በዛሬው እለት እንዳስታወቀውም ከካዛብላንካ ወደ ዶሃ የሚደረጉ 30 በረራዎች ማክስኞ እና ረቡዕ ይደረጋሉ ብሏል፡፡
አየር መንገዱ ይህን ያደረገው ሞሮኮዊያን ዜጎችን ለማሰደስት እና ሀገሪቱ አፍሪካን ወክላ በአለም ዋንጫው ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀሏን ተከትሎ ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ሞሮኮ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ስትሆን በመጪው ረቡዕ ፈረንሳይን እንደምትገጥም ሲጂቲኤን በዘገባው ጠቁሟል።
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች