አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለበርካታ ዓመታት የጤናውን ዘርፍ በመደገፍ የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥር 30/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለበርካታ ዓመታት የጤናውን ዘርፍ በመደገፍ የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ገልጸዋል።
ድርጅቱ የጤናን ሥራ ሊያግዙ የሚችሉ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፣ አልትራሳወንድ፣ ወንበርና ጤረጴዛዎችን ለደቡብ ኦሞ ዞን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በጤና ኤክስቴንሽን ተግባር ውጤታማ ለሆኑ እናቶች ጤና ኤክስቴንሽኖችና ለጤና ባለሙያዎች ሌሎችም ዕወቅና ሰጥቷል።
በድጋፉ የአምረፍ ሄልዝ አፍሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስተባባሪ ተወካይ መስፍን ማቲዮስ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ በጤናው ዘርፍ በተለይም በደቡብ ኦሞ ዞን በርካታ ሥራዎችን ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው ከፕሮጀክቶቹ አንዱ በሆነውና እየሰራ ባለው አዲሱን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በመደገፍ ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ድጋፍና ውይይት መሆኑን አንስተዋል።
አጠቃላይ የድጋፉ ወጪ 4 ሚሊየን 4 መቶ ሺህ 592 ብር በላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በንግግራቸው፤ የአምረፍ ሄልዝ አፍሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለበርካታ ዓመታት የጤናውን ዘርፍ በመደገፍ የማይተካ ሚና እየተወጣ መሆኑን አመላክቷል።
ፍትሐዊነትንና ትኩረት የሚሹ አካባቢዎች ላይ በማተኮር በተለይም በእናቶች ጤናና እንክብካቤ ሥራዎች ጋር ተያይዞ የመንግስት ቁርጠኝነት ተደምሮ ድርጅቱ ቀጥተኛ ድጋፍ እንደነበረው አንስተው ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
ድጋፎችን ለታለመለት አላማ በማዋል በትኩረት እንዲሰሩም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው የየወረዳው ተወካዮችም ድርጅቱ ባደረገው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አጋዥ መሆናቸውንና ለታለመላቸው አላማ በማዋል እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
ዕወቅናውን ያገኙ ተሳታፊዎችም ከዚህ በበለጠ በመስራት ህይወታቸውን እንደሚመሩ ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ከመግፋፋት በመውጣት የመደመር ዕሳቤን በማጎልበት በህዝቦች መካከል ያሉ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 518 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ውጤታማ የሆነ ስራ የሰራ አካባቢ ተጨማሪ ፕሮጀክት የማግኘት ዕድል አለው – ሚ/ር ዴኤታ የትምጌታ አስራት