ከእርሻ መሬት መጠቀሚያ ግብር 20 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  ሀዲያ ዞን የጎምቦራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ ቤት አስታወቀ

ከእርሻ መሬት መጠቀሚያ ግብር 20 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  ሀዲያ ዞን የጎምቦራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ ቤት አስታወቀ

በወረዳው የእርሻ መሬት መጠቀሚያ ግብር የሚከፍሉ ከ14 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መኖራቸውም ተገልጿል ።

የጎምቦራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ከበደ እንደገለጹት ወረዳው የሚያመናጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ ከህብረተሰቡ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ ይገኛል።

በወረዳው በ2017 በጀት አመት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤታዊ የገቢ አርዕስቶች 157 ሚሊዮን 40 ሺህ 8 መቶ ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ባለፉት 6 ወራት 62 ሚሊዮን 381 ሺህ 906 ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።

በወረዳው ከእርሻ መሬት መጠቀሚያ ግብር 20 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል ያሉት አቶ ዳዊት እስከአሁን 4 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል ።

አቶ ደመቀ ዴታሞ በሀቢቾ  ከተማ በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ግብር ከፋይ ሲሆኑ በግብር የሚሰበሰበው ገንዘብ ለሀገር ልማት የሚውል በመሆኑ ግብርን በወቅቱ እየከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሌላኛዋ የእርሻ መሬት መጠቀሚያ ግብር ከፋይ የሆኑት አርሶ አደር ወ/ሮ አዳነች ኤራሞ በበኩላቸው አርሰው ከሚጠቀሙት መሬት እንዲከፍሉ የተወሰነላቸውን ግብር መክፈላቸዉን ተናግረዋል ።

ዘጋቢ :ተሻለ ከበደ -ሆሳዕና ጣቢያችን