ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት የተበረከተላቸው÷ “አፍሪካ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት” በሚል መሪ ሐሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንት እና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙ ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ላይ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ስታስጀምር፣ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢልየን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ ከታቀደው ግብ አልፋ በመላ ሀገሪቱ 25 ቢልየን ችግኞች በመትከል የአራት ዓመት ዕቅዷን አሳክታለች። በዚህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለደን መልሶ ልማት ላደረገችው አስተዋጽዖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝታለች።
More Stories
አሊያንስ ኮሌጅ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት የሀገሪቱን ዕድገት ለማፋጠን የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታወቀ
በ2018 የትምህርት ዘመን ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመጡ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዉ መቀጠል ይኖርባቸዋል – የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደ
ተማሪዎች በወቅቱ ትምህርት ቤት ቀርበዉ እንዲመዘገቡ ወላጆች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ