ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ረገድ ያስመዘገበችው ድልና ስኬት የመልማት ፍላጎቷ አይነተኛ መገለጫ መሆኑ ተገለፀ
የለውጡን መንግስት ተከትሎ የብልጽግና ፓርቲ ካስመዘገባቸው ስኬታማ ተግባራት መካከል፥ እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚና የህዝብ ቁጥር የሚመጥን የባህር በር በሌለበት ዘላቂነት ሊኖረው እንደማይችል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለጹ።
ከ120 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላት ኢትዮጵያ በፈጣን እድገት ላይ ያለው ኢኮኖሚ ያለ ባህር በር ዘላቂነት የለውም ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በተካሔዱ የዲፕሎማሲ ስራዎች በተገኘው ውጤት፥ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ላለው ፈጣን እድገት የባህር በር እንደሚያስፈልጋት በብዙዎች የዓለም መንግስታት ዘንድ ቅቡልነት እያገኘ መምጣቱን ጠቁመው፥ እየገነባን ካለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና ከሀገራችን የለውጥ ፍላጎት ጋር የባህር በር ከፍተኛ መስተጋብር ያለው በመሆኑ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተገኘው ስኬት የመልማት ፍላጎታችን ማሳያ ነው ብለዋል።
ይህም የጠቅላይ ሚኒስትሩን የመሪነት ብቃት፣ ቁርጠኝነትና ድፍረት የታየበት የአመራር ስትራቴጂ፥ ዓለም በእርግጥም ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል ወደሚል ድምዳሜ እንዲመጣ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ስኬት፥ ከአንደኛው የብልጽግና ጉባኤ ማግስት የተገኘ የዲፕሎማሲው ውጤታማነት ማሳያ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለም ህዝብ ግማሹን የሸፈኑ ከመሆናቸው ባለፈ ከፍተኛ የዓለም ኢኮኖሚ በሚያንቀሳቅሱ ስብስብ ውስጥ መካተቷ፥ በዓለም ደረጃ የኢትዮጵያን ተጽዕኖ የሚያጎላው መሆኑን ተናግረዋል።
በዲፕሎማሲው መስክ ለጎረቤት ቅድሚያ የሚሰጥ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና ዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ አቅጣጫ የሚከተል በመሆኑ ሀገራችን በዓለም አቀፍ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ተደማጭነትን ከፍ ማድርግ የሚያስችሉ ውጤቶች እየተመዘገ መምጣቱን አውስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከጎረቤት አገራት ጋር ያለንን ሁሉን አቀፍ ግኙነት በማጠናከር ለሰላምና ጸጥታ፣ ለኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ትስስር ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየተደረገ ያለው ጥረት፥ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ላይ ድል መቀዳጀቷን የሚያመላክት ነው ብለዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ለሀገራችን ፈጣን ኢኮኖሚ ፍላጎት ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጥ የሚችል እና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብር በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራዊ ክብርን የሚያስጠብቅ፣ የዜጎችን መብት ክብርና ደህንነት የሚያረጋግጥ ለመሆኑ አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
የተመዘገቡ አበረታች ዉጤቶችን በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ
በዳዉሮ ዞን በዘንድሮ በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት 40 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ልማት መምሪያ አስታወቀ
በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ተግባራት የህብረተሰቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄ መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ተናገሩ