አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን፣ 8ኛ አስቸኳይ ጉባዔ አቶ ዮሐንስ አበጋን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።
አዲሱ ዋና አስተዳዳሪ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
አቶ ዮሐንስ አበጋ ቀደም ሲል የአንሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩ ናቸው።
ዘጋቢ:- በየነ ሰላሙ ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)