የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ አመራሮች፣ ሰራተኞች እንዲሁም ለዞንና ለልዩ ወረዳ የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ከፍል ቡድን መሪዎች በስነ-ምግባር እና በግዥ አስተዳደር ስርዓት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
የስልጠናውን መድረክ በንግግር የከፈቱት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሃመድ ኑርዬ፤ መንገድና ትራንስፖርት ሁሉንም የሚመለከቱ በመሆናቸው ዘርፉ በመልካም ስነ-ምግባር እና ከሙስና በፀዳ መልኩ እንዲመራ የጋራ ጥረት የሚጠይቅ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።
በመድረኩ በተለያዩ አርእስቶች የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ እንዳልካቸው ደሳለኝ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ለከተማ ዕድገትና ልማት የህብረተሰቡ ተሳትፎ የጎላ ድርሻ እንዳለው ተጠቆመ
በደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ የምሁራን ምክክር ተካሄደ
ምክር ቤቱ አረንጓዴ አሻራን የሚያጠናክር እና የተጎሳቆለ መሬትን እንዲያገግም የሚያስችል አዋጅ አፀደቀ