19ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን አስመልክቶ በዞኑ በሁሉም አቅጣጫዎች ፀጥታን የማስከበር ስራ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ የጋሞ ዞን ፖሊስ አስታወቀ
እንግዶች ከበዓሉ ጎን ለጎን ያለ ስጋት የጋሞ ዞን የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙም ይደረጋል ተብሏል።
የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ጋፋሮ ቶማስ፤ በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ፖሊስ ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ስራ ማከናወኑን ተናግረዋል።
ከሰላም ወዳዱ የከተማው ህብረተሰብ ጋር ቅንጅታዊ ስራ መሠራቱን ያወሱት ምክትል ኢንስፔክተር ጋፋሮ፤ ህብረተሰቡ ራሱን፣ አካባቢውን እና እንግዶችን እንደሚጠብቅ ክልላዊና ሀገራዊ መድረኮች በአርባምንጭ ከተማ በተካሄዱበት ወቅት በተግባር ማሳየቱን አንስተዋል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደበበ ኡንቶ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የኢትዮጵያን ህዝቦች የሚያቀራርብ፣ ብዝሃነት የተከበረበትና እኩል ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ቀን መሆኑን አውስተዋል።
በመሆኑም በዞኑ በሚገኙ ሁሉም መዋቅሮችና በአርባምንጭ ከተማ 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር የተለያዩ የዝግጅት ተግባራት ተከናውነዋል ሲሉ አረጋግጠዋል።
በዞኑ በሁሉም አቅጣጫ ፀጥታ የማስከበር ስራ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዉ፤ ወደ ዞኑ የሚመጡ እንግዶች ያለሥጋት በሁሉም አካባቢዎች መንቀሳቀስ እንዲችሉ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ