ሩድ ቫኔስትሮይ የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ሆኖ በይፋ ተሾመ
ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ሩድ ቫኔስትሮይ የእንግሊዙ ክለብ ሌስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል።
በቅርቡ ከማንቸስተር ዩናይትድ ግዚያዊ ዋና አሰልጣኝነት የለቀቀው ቫኔስትሮይ በኪንግ ፓወር እንደ አውሮፓውያኑ እስከ 2027 ድረስ የሚያቆየውን ኮንትራት መፈረሙን ክለቡ አሳውቋል።
ሩድ ቫኔስትሮይ ከ5 ቀናት በፊት ከሃላፊነት የተሰናበቱትን ስቲቭ ኩፐርን በመተካት ነው ቀበሮዎችን የተረከበው።
በሌስተር የመጀመሪያ ጨዋታውን የፊታችን ማክሰኞ በኪንግ ፓውር ስታዲየም ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር የሚካሄደውን ጨዋታ በመምራት ይሆናል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ከፌነርባቼ ሃላፊነት ተነሱ
ዣቪ ሲሞንስ ወደ ቶትንሃም ለመዛወር የጤና ምርመራውን አጠናቀቀ
ዣቪ ሲሞንስ አዲስ ፈላጊ ክለብ አገኘ