በ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ከ241 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ተግባራት መከናወኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማጠቃለያ እና እውቅና መድረክ እየተካሄደ ነወ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊው አቶ ሉምባ ደምሴ እንደተናገሩት ካለፉት 10 ዓመታት ወዲህ በሀገር አቀፍ ደረጃ መንግስት ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ልዩ ትኩረት ሰጥቷል::
በክልሉም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ ለጉልበት ብዝበዛ ሰለበ የሆኑ ህፃናትንና ሌሎችን በመደገፍና በመንከባከብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል::
በ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ8 ዋና ዋና ተግባራት ከ241 ሚሊየን 33 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ተግባራት መከናወኑንም አቶ ሉምባ አመላክተዋል::
በመድረኩም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትልና የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ሳሙኤል፤ በ2016 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል::
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሉምባ ደምሴ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራን ጨምሮ ከሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳ የመጡ የመምሪያ ኃላፊዎችና በጎ አድራጊዎች እየተሳተፉ ናቸው::
ዘጋቢ: በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው