ቼልሲ ሌስተርን አሸነፈ
በ12ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ ከሜዳው ውጪ ሌስተር ሲቲን የገጠመው ቼልሲ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የቼልሲን የድል ግቦች ኒኮላስ ጃክሰን እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ ከመረብ አሳርፈዋል።
ሌስተርን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ጆርዳን አየው በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
ኒኮላስ ጃክሰን በውድድር ዓመቱ 7ኛ የሊግ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።
ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ ነጥቡን ወደ 22 ከፍ በማድረግ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ሌስተር ሲቲ በ10 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ፕሪሚዬርሊጉ መካሄዱን ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ አርሰናል ከኖቲንግሃም ፎረስት፣አስቶንቪላ ከክርስቲያል ፓላስ፣በርንማውዝ ከብራይተን፣ ኤቨርተን ከብሬንትፎርድ እና ፉልሃም ከዎልቭስ ይጫወታሉ።
እንዲሁም ምሽት 2ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ቶትንሃምን ያስተናግዳል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
2ኛው የየም ዞን ስፖርት ሻምፕዮና በሣጃ ከተማ እየተካሄደ ነው
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ