በቀቤና ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የማስ ስፖርት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ፡ ሕዳር 08/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቀቤና ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የማስ ስፖርት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደርና ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከልዩ ወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁትና በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የማስ ስፖርት መርሃ ግብር ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ መነቴ ሙንዲኖ፣ የልዩ ወረዳው አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ወጣቶችና ሌሎችም የልዩ ወረዳው የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች