የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 08/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርት ተካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የአሪ ዞንና የጂንካ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስፖርት ባለሙያዎችና የከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደፋሩ እና የአሪ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ በጋራ እንደገለፁት የፓርቲው 5ኛ ዓመት ክብረ በዓል “የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኩኔቶች እንደሚከበር ጠቅሰው፤ ተከታታይነት ያለው ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የዚሁ አካል መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የአሪ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያየህብረተሰብ ተሳትፎና ውድድር ቡድን መሪ አቶ አየናቸው ጥላሁን እንዳስረዱት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር መምሪያው እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ጤናማ ማህበረሰብን ለማፍራት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑን በስፖርቱ የተሳተፉ አካላት ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 6ኛ ዙር መርሐግብር 9 ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ
ሩድ ቫኔስትሮይ የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ሆኖ በይፋ ተሾመ
ሊቨርፑልና ሪያል ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊግ ታላቅ ጨዋታን ዛሬ ምሽት ያካሂዳሉ