በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋፍ አሰጣጥና አስተዳደር ዙሪያ ለዞንና ልዩ ወረዳ አመራሮች እንዲሁም ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በወልቂጤ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ስልጠናው የሚሰጠው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢንተርፕሪነር ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ሲሆን ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተጠቁሟል።
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሙዲን ሁሴን፤ የሳይንስና ፈጠራ ስራዎችን በአግባቡ በማልማትና በማስፋት እንደሀገር አለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።
የፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕና ኢኖቬሽን ኢኮሲስተም እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች በማጠናከር የዘርፉን አቅም በማሳደግ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ስልጠናው የሳይንስ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ አዱኛ ትዕዛዙ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በራስ አቅም ጀምራ መጨረስን ያሳየችበት ዳግማዊ የአድዋ ድል የሆነ እና የወል ትርክትን ያፀና ፕሮጀክት መሆኑን የእኖር ወረዳ አስተዳደር ገለጸ
በጋሞ ዞን ውስጥ ያሉ የሶስቱን ነባር ብሔረሰቦች ዘመን መለወጫ በዓላቸውን ጨምሮ ቋንቋን፣ ታሪክንና ባህላዊ ዕሴቶችን በጥናትና ምርምር በማጉላት ለተጠቃሚነት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተገለፀ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ አስተዳደር ሁለት ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ዘመናዊ ሆቴሎችን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ