አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት ያስችላል የተባለ ውይይት እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ሕዳር 03/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት ያስችላል የተባለ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው ውይይት የክልልና የፌደራል የዘርፉ አካላት እየተሳተፋ ነው።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ አክመል አህመዲን፤ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የህግ ስርዓት ቢዘረጋም የዜጎች ሞት፣ እንግልትና ጥቃት አሁንም አልቆመም ብለዋል።
ችግሩ ዓለም አቀፋዊ በመሆኑ ድንበር ዘለል ትብብርን ይጠይቃል ያሉት ሀላፊው፤ አዋጆችን በወጉ መተግበርና የግንዛቤ ፈጠራ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የተሻለ ገቢ ፍለጋ እና የህገ ወጥ ደላሎች ተፅዕኖ ዜጎችን ለእንግልት እየዳረገ ነው ያሉት አቶ አክመል፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የችግሩ ገፈት ቀማሽ በመሆኑ የጠነከረ የትብብር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በኢፌዲሪ የፍትህ ሚኒስቴር የፍልሰት ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ዮሀንስ ሲሳይ በበኩላቸው፤ ችግሩን ለመከላከል የወጡ ህጎችን በወጉ መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ባየ በልስቲ
More Stories
ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ
የትምህርት ጥራትና ውጤት መሻሻል ዙሪያ የሚተገበሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳሰበ